የፍቅር ክሊኒክ የቀዶ ጥገና ርዕሰ ጉዳይ
Description
የፍቅር ክሊኒክ የቀዶ ጥገና ርዕሰ ጉዳይ
…21 ዓመቴ ነው፡፡ ከፍቅረኛዬ ጋር አንድ ዓመት ከቆየን በኋላ ቃል ተገባብተን እኔ ከኢትዮጵያ ውጭ ሄድኩ፡፡ እንደሄድኩ እርሱ ከቀድሞ ፍቅረኛው ጋር ድጋሚ ፍቅር እንደጀመረ ሰማሁ፡፡ ከዓመት በኋላ ለእረፍት መጥቼ ስለጉዳዩ ስጠይቀው ‹ከእርሷ ጋር እንደተገናኘ ግን ምንም አይነት ነገር እንዳላደረጉ› ነገረኝ፡፡ ስለተናደድኩ ብዙ ሳላወራው ተመለስኩ፡፡ እዚያም ሄጄ ድጋሚ ሌላ ፍቅረኛ እንደያዘ ሰማሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ አሁን ደጋግሞ እየደወለ ይቅርታ እንዳደርግለትና አብረን እንድንሆን እየጠየቀኝ ነው፡፡ እምቢ ብለውም ‹ስታገቢ ካላየሁ በስተቀር ተስፋ አልቆጥርም› ብሎ ይጨቀጭቀኛል፡፡ ይቅርታ አድርጌለት አብሬው ልሁን ወይል ልለየው?
- ሰላም
Comments